Fana: At a Speed of Life!

የፌደራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ የሰላምና ፀጥታ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በወቅታዊ ሀገራዊ የሰላም እና የፀጥታ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉትን ውይይት በዛሬው ዕለት ጀምረዋል።

የውይይት መድረኩ “ተቋማዊ አቅምን በመገንባት ስኬቶቻችንን እናጠናክራለን” በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ነው፡፡

እንደ ሀገር የተገኙ ስኬቶችን አጠናክሮ ለመቀጠል እንዲሁም የሚስተዋሉ ችግሮችን እልባት እንዲያገኙ አቅጣጫ የሚቀመጥበት ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

አመራሩም ድሎችን የማፅናትና ፈተናዎችን የመሻገር ታሪካዊ ተልእኮ ተቀብሎ በመሰማራት ለኢትዮጵያ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚጠበቅበትን በጎ አሻራ እንዲያስቀምጥ ብሎም ውስጣዊ አንድነቱን በማጠናከር ፈተናዎችን በድል የመሻገር አቅም የሚያዳብርበት ይሆናልም ተብሏል።

መድረኩ ለተከታታይ ሦስት ቀናት የሚቀጥል ሲሆን ፥ በርካታ ሰነዶች ቀርበው ውይይት እንደሚደረግባቸው ከብልጽግና ፓርቲ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.