Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያና ኢኳቶሪያል ጊኒን የተፈጥሮ ሃብቶች መሰረት ባደረጉ ፕሮጀክቶች ላይ ባለሀብቶች እንደሚሰማሩ ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሁለቱን ሀገራት የተፈጥሮ ሃብቶች መሰረት ያደረጉ ፕሮጀክቶች በመለየት በዘርፉ ባለሀብቶች እንደሚሰማሩ የኢኳቶሪያል ጊኒ የፕላንና ኢኮኖሚ ዳይቭርሲፊኬሽን ሚኒስትር ጋብርኤል ኦብያንግ ገለጹ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከኢኳቶሪያል ጊኒ የፕላንና ኢኮኖሚ ዳይቭርሲፊኬሽን ሚኒስትር ጋብርኤል ኦብያንግ ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሂደዋል፡፡

በዚህ ወቅት ጋብርኤል ኦብያንግ እንዳሉት ፥ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሁለቱን ሀገራት የተፈጥሮ ሃብቶች መሰረት ያደረጉ ፕሮጀክቶች በመለየት በዘርፉ ባለሀብቶች እንዲሰማሩ ይደረጋል፡፡

በተጨማሪም በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ያሉ ምቹ ሁኔታዎችና አማራጮች ዙሪያም ውይይት መደረጉን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

በውይይቱም ፥ የሁለቱ ሀገራት የልምድ ልውውጥና የኢኮኖሚ ትስስር ወዳጅነትን ከማጠናከር ባለፈ ለአምራች ኢንዱስትሪው ዕድገት ወሳኝ ሚና እንዳለውም ተገልጿል።

#Ethiopia #EquatorialGuinea

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.