Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል ሲከናወን የቆየው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ወደ ሥነ ሕይወታዊ ሥራ ተሸጋገረ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ላለፈው አንድ ወር ሲከናወን የቆየው የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ወደ ሥነ ሕይወታዊ ሥራ መሸጋገሩ ተገለጸ፡፡

የተፈጥሮ ሃብት ሥራውን ወደ ሥነ ሕይወታዊ ጠቀሜታ ማሸጋገር የተፈጥሮ ሀብት ሥራው ትኩረት መሆኑ ተገልጿል፡፡

የሥነ ሕይወት ሀብት ልማት ሥራው ለቀጣዮቹ ሦስት ወራት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ነው የተመለከተው፡፡

ሕብረተሰቡ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ያሳየውን ትጋት በሥነ ሕይወታዊ ሥራው በመድገም አካባቢውን እየታደገ እራሱን ተጠቃሚ እንዲያደርግ ተጠይቋል።

በክልሉ በአማካይ ለ24 ቀናት በ8 ሺህ 575 ነባር እና በ8 ሺህ 596 አዲስ ተፋሰሶች ላይ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው መከናወኑ ተገልጿል፡፡

በአጠቃላይ ከ331ሺህ ሔክታር በላይ በሥራው ተደራሽ መደረጉን የክልሉ ግብርና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አልማዝ ጊዜው ተናግረዋል፡፡

በተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራው ከ4 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ ሕዝብ በጉልበት መሳተፉን እና ይህም 3 ቢሊየን ብር እንደሚገመት ነው ኃላፊዋ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት የተናገሩት፡፡

በኤሊያስ አንሙት

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.