Fana: At a Speed of Life!

በመጪው ክረምት በጎርፍ አደጋ ጉዳት እንዳይደርስ እየተሠራ ነው ተባለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በ2015 ዓ.ም የክረምት ወቅት በጎርፍ አደጋ በሰውና ንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ገለጸ፡፡

በኮሚሽኑ የአደጋ ስጋት ቅነሳ ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር ይክፈለው ገ/መስቀል በሰጡት መግለጫ÷ 219 የእሳት፣ 180 የጎርፍ እና 104 የመሬት መንሸራተት የአደጋ ተጋላጭነት እንዳለ በዳሰሳ ጥናት መጠቆሙን ገልጸዋል፡፡

የሚያጋጥሙ ድንገተኛ አደጋዎችን ደረጃ በመለየት የአደጋ ቅነሳ ሥራዎች እየተከናወኑ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡

ለአደጋ ታጋላጭ ተብለው ከተለዩ 284 ቦታዎች ውስጥ 168 አስቸኳይ መፍትሔ እንደሚሹም አመላክተዋል፡፡

በተለይም 55 ቦታዎች ልዩ ትኩረት እንደሚፈልጉ ታምኖበት በዚሁ አግባብ እየተሠራ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የጎርፍ አደጋ ተጋላጭነትን ለመቀነስም ሕብረተሰቡ የደረቅ ቆሻሻ አወጋገዱ የአደጋ ተጋላጭነትን በማያስከትል ሁኔታ እንዲሆን ጠይቀዋል፡፡

በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት በአዲስ አበባ ከተከሰቱ 206 አደጋዎች 131 በእሳት አደጋ መከሰታቸውን ተገልጿል፡፡

በሜሮን ሙሉጌታ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.