Fana: At a Speed of Life!

በሽሮና በርበሬ አደንዛዥ ዕፅ ደብቆ ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ ሞክሯል የተባለ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሽሮና በርበሬ ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ ደብቆ ወደ ውጭ ሀገር ለመላክ የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 መርካቶ ጣና የገበያ ማዕከል አካባቢ በሚገኘው ፖስታ ቤት ነው ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ዋለው፡፡

ተገማች ባልሆነ ሁኔታ ካናቢስ የተሰኘውን አደንዛዥ ዕፅ በሽሮና በርበሬ ውስጥ ደብቆ በካርቶንና ፌስታል አሽጎ ወደ ለንደን በኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት ለመላክ ሙከራ ሲያደርግ ከነኤግዚቢቱ መያዙ ተገልጿል፡፡

ምርመራ መጀመሩንም የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.