Fana: At a Speed of Life!

ለፍቅር ህይወት መበላሸት እርስዎ ምክንያት መሆንዎን የሚያመላክቱ ሁኔታዎች

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 15 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ብዙዎች በፍቅር ሕይወት ውስጥ ውጣውረድ ሲያጋጥማቸው ወደ እራሳቸው ከመመልከት ይልቅ ችግሩን የሌላኛው ወገን አድርገው ለመፍትሄ ሲባዝኑ ይስተዋላል፡፡

የሥነ ልቦና ባለሙያዎችም ይህ አይነቱ እሳቤ ምናልባትም ከራስ ወዳድነት እኔ ሁሉንም ነገር ልክ ነኝ ብሎ ከማሰብ እንደሚመነጭ ይናገራሉ።

እንደ ባለሙያዎቹ ገለጻ በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ለፍቅር ግንኙነት መሻከር አልያም መፍረስ እርስዎ ምክንያት ሊሆኑ ይችላሉ።

እንዴት ካሉ እነዚህ ምክንያቶች ለዚህ ችግር እርስዎ ተጠያቂ መሆንዎን የሚያመለክቱ ናቸው÷

1. የፍቅር አጋርዎን ፍጹምና ምሉዕ አድርገው ማሰብ

ለራስዎ የሚገባዎትን ክብር አለመሥጠት፣ በፍቅር ሕይወት ውስጥ አበርክቶ እንዳለዎት መዘንጋት፣ ሁሉንም ውሳኔ ለትዳር አጋርዎ አሳልፎ መስጠትና ይህን ተከትሎ በሚመጣ ነገር መፀፀት።

በአጸፋው የትዳር አጋርዎ እነሱ ምሉዕ እና ትክክል እንደሆኑ እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል ይህ መሆኑ ደግሞ አጋርዎ በበላይነት ሥሜት እንዲሞሉ ያደርጓቸዋል – ለዚህ ምክንያቱ እርስዎ ስለሆኑ ማንንም ተጠያቂ አያድርጉ፡፡

እርስዎ ለትዳር አጋርዎ እራስዎን ባቀረቡበት ልክ በእርሳቸው ዓይን ያነሱ ሆነው ታይተዋል፤ ከዚህ አንጻርም በትዳር አጋርዎ አካባቢ ለሚናገሩት ሐሳብና ለሚፈፅሙት ድርጊት በጣም መጠንቀቅ ይጀምራሉ፡፡

ይህም የውሳኔ ሰጪነት ሚናን ብሎም ተቀባይነትዎን ያሳጣዎታል።

በራስ አለመተማመን፦ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በራሱ የሚተማመን ሰው መልካም የፍቅር ግንኙነት ይኖረዋል፡፡

የራስን ጉድለት አጉልቶ ማየት እና ጉድለትን ለመሙላት በፍቅር አጋር ላይ አብዝቶ ጥገኛ መሆን ግንኙነትዎን በራስዎ እጅ አደጋ ውስጥ ማስገባት ነው፡፡

የፍቅር ግንኙነቶች ጤናማ የሚባሉት ከሁለቱም ወገን የሚታዩ የፍቅር መገለጫዎች እና ሥሜቶች መታየት ሲችሉ ነው፡፡

ግንኙነቶች አለመጎዳታቸውን ለማረጋገጥ ያንን ስሜት ከፍቅር አጋርዎ ለማስተዋልዎ እርግጠኛ ይሁኑ ፤ ከተጠራጠሩ ለማስተዋል ጊዜ ይስጡ፡፡

2. ከፍቅር አጋሮቻቸው ጋር የተለያዩ ሰዎችን የራስ ለማድረግ ጊዜ ማጥፋት

ሰዎች የፍቅር ግንኙነታቸው አደጋ ውስጥ ሲወድቅ እና ሲቋረጥ ጊዜ ወስደው ማሰብ እና ዕልባት በመስጠት መቋጨት ስለሚፈልጉ አብረን እንሁን ወይም ያለፈውን እርሳው/እርሽው በሚል ሃሳብ መጫን አይገባም።

በትክክል ግንኙነት ከእነርሱ ጋር ለመመስረት ፍላጎት ካለዎት ደግሞ ይህን ያድርጉ

. ከእነርሱ ጋር ሲሆኑ አብዝተው ስላለፈ ትዳራቸው የሚያነሱ ከሆነ ከትዝታቸውና ካለፈ ቁስላቸው ገና ያልዳኑ በመሆኑ ጊዜ ይስጧቸው፡፡

. በተለይ ስላለፈ ግንኙነታቸው አሉታዊ ነገር የሚያወሩ ከሆነ ለአዲስ ግንኙነት ገና ዝግጁ እንዳልሆኑ መረዳት ይኖርብዎታል፡፡

. ከትዳራቸው ከተለያዩ ሰዎች ጋር ፍቅር ሲጀምሩ ከእርስዎ ጋር ለመቀጠል የውሳኔ ችግር ሚያስተውሉባቸው ከሆነ ምናልባትም ከእርስዎ ጋር ፍቅር የጀመሩት ሌላ ፍቅረኛ መያዝ እንደሚችሉ ለተለዩት ሰው ማሳየት ስለሚፈልጉ ብቻ ሊሆን ይችላል፡፡

ስለሆነም በትክክል ከእርስዎ ጋር ፍቅር ለመጀመር ፍላጎት እንዳላቸው ያጢኑና ይወስኑ ፍቅር እንጀምር ሲሉ እሺታን ስላገኙ ብቻ ግንኙነት መጀመር ችግር የበዛበት የፍቅር ጊዜን ሊያስከትል ስለሚችል ይጠንቀቁ።

3. አብራችሁ ስለሆናችሁ ብቻ ትክክለኛ ፍቅር እንዳለ ማሰብ

ምናልባት አብራችሁ ጊዜ ማሳለፍ፣ ሲኒማ ቤት መግባት፣ ሽርሽር ማድረግ እና እየተገናኙ የእራት ግብዣም ይሁን በፍቅር ጨዋታ ማሳለፍ ብቻውን ትክክለኛ ፍቅርን አይገልጽም።

አንዳንድ ጊዜ ምናልባትም ከፍቅር አጋርዎ በአካል እንጅ በመንፈስ የተለያዩ ጊዜን አብሮ ለማሳለፍና ለፍቅር ጨዋታ ብቻ የምትገናኙ ሊሆን ይችላል፤ ይህን አደረጉ ማለት ግን በመሃላችሁ ፍቅር አለ ብሎ እርግጠኛ ሆኖ መደምደም ትክክል አለመሆኑን የስነ ልቦና ባለሙያዎች ይገልጻሉ።

እውነተኛ ፍቅር ውስጥ ነን ወይስ ለፍቅር ጨዋታ ብቻ ነው የምንገናኘው የሚለውን ለመለየትደግሞ ባለሙያዎቹ ይህን ሞክሩት ይላሉ።

.የጋራ የሆኑ ስሜቶችንና ፍላጎቶችን ማገናዘብ፦ ከፍቅር ጨዋታ ውጪ ያላችሁ ግንኙነት መልካምና በጨዋታና በጋራ ስሜት ከተሞላ አጋርዎ ከዛ ያለፈ በህይወት መንገድዎት አብሮ ሊዘልቅ ይችላል።

ሁልጊዜም ራስዎን ይግለጹ፦ ምናልባት ከአጋርዎ ጋር ተመሳሳይ ዕሳቤና ስሜት ውስጥ ነኝ ብለው ካሰቡ ስሜትዎን ከመግለጽ አይቆጠቡ።

በዚህ ወቅት ታዲያ ከጀመራችሁት ግንኙነት ምን እንደሚጠብቁና ረጅም ርቀትን መጓዝ እንደሚፈልጉ ማስረዳት።

ይህን ሲያደርጉ ታዲያ እንዲያስቡበት በቂ ጊዜና ቦታ መስጠት ብሎም ከእርስዎ ፍላጎት ባለፈ ከአጋርዎ ሃሳብ ጋር ሊስማሙ እንደሚችሉ ማሳየትም መልካም ነው።

ከፍቅር ጨዋታ ውጭ ጊዜ ይኑራችሁ፦ ያለዎት ግንኙነት ከፍቅር ግንኙነት ያለፈ ይዘልቃል ወይ ? የሚል ጥያቄ ካለዎት ከቤት ውጭ ለሻይ ቡና፣ ለመዝናናት እና አብሮ በመጫዎት እያሳለፉ ሁኔታዎችን መገምገም ይልመዱ።

የተግባቦት አቅምዎን ይመልከቱ፦ በቅርቡ ይፋ የተደረገ ጥናት እንደሚያመላክተው በበቂ እና በግልጽ የሚነጋገሩና ተግባቦት ላይ ቀጥተኛ የሆኑ ጥንዶች በፍቅር ህይወታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ያመላክታል።

ይህም ስሜታቸውን ሌላውን ሳይጎዳና ሳያስቀይም በቀጥታና በግልጽ መናገር መቻላቸው ሳይደባበቁ እንዲጓዙ ስላስቻላቸው መሆኑን ነው ሳይኮሎጂ ቱ ደይ ያወጣው ዘገባ የሚያመላክተው።

በጉዳዩ ላይ በርካታ መፅሐፍትን የጻፉት የፍቅር ስነ ልቦና ባለሙያውና ተመራማሪው ዶክተር ማርክ ትሬቨርስ የፍቅር ህይወትን ወደ ቀጣዩ ደረጃ ለማሳደግ በሚል የፍቅር ጨዋታን አማራጭ ማድረግ ከስነ ልቦና ቁጭት ያለፈ ፋይዳ የሌለውና የማይመከር ነው መሆኑን ያስረዳሉ።

በዓለማየሁ ገረመው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.