Fana: At a Speed of Life!

ቆላማና ዝናብ አጠር አካባቢዎችን ያማከሉ ፖሊሲዎች ሊቀረጹ ይገባል – የግብርና ባለሙያዎች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጲያ ቆላማ እና ዝናብ አጠር አካባቢዎችን ያማከሉ ፖሊሲዎች ሊቀረጹ እንደሚገባ የግብርና ባለሙያዎች ተናገሩ።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉ የግብርና ባለሞያዎች ፥ የሚወጡ ፖሊሲዎች አካባቢዎቹን ያማከሉ ባለመሆናቸው ፣ ተግባራዊ ሲደረጉ ውጤታማ እንዳልሆኑ ያነሳሉ።

የቦረና ዩኒቨርሲቲ መምህርና ተመራማሪ አቶ ገልማ ዋቆ ፥ በሀገር ደረጃ የሚወጡ ፖሊሲዎች የአካባቢዎቹን ባህልና አኗኗር ዘይቤን ያካተተ ባለመሆኑ መሬት ላይ ወርደው ተግባራዊ ሲደረጉ ውጤታማ አይሆኑም ብለዋል፡፡

በጅማ ዩኒቨርስቲ ግብርና እና እንስሳት ህክምና ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ ዶክተር አዱኛ እንየው በበኩላቸው ፥ ፖሊሲዎች ከወረቀት በዘለለ ወደ ተግባር ባለመቀየራቸው ችግሩ መከሰቱን ያነሳሉ፡፡

በተደጋጋሚ ጊዜ ከፍተኛ ድርቅ የተከሰተ ቢሆንም የተሰጣቸው ትኩረት አነስተኛ እንደሆነ ነው ባለሙያዎቹ የሚገልጹት።

የዝናብ እጥረት ከመከሰቱ በፊትም ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ስራዎች መሰራት እንደሚገባም ነው ባለሙያዎቹ ያሳሰቡት።

ምሁራኑ ለተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ሥራ ትኩረት መሰጠት አለበት ሲሉም በአጽንዖት ተናግረዋል፡፡

እንደ ምሁራኑ ገለጻ ፥ ድርቅን ተቋቁሞ ለመቀጠል ከእንስሳት እርባታና ከግብርና ስራ በተጨማሪ በንግድ እና ኢንዱስትሪ ስራዎች ላይ መሰማራት ይገባል።

በአልማዝ መኮንን

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.