Fana: At a Speed of Life!

ሰሜን ኮሮያ በርካታ የአጭር ርቀት ሚሳኤሎችን የማስወንጨፍ ሙከራ ማድረጓ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰሜን ኮሮያ በርካታ የአጭር ርቀት ሚሳኤሎችን የማስወንጨፍ ሙከራ ማድረጓ ተገልጿል።

የኮሮናቫይረስ ዓለማችንን ባስጨነቀበት በዚህ ወቅት ፒዮንግያንግ ግን የጦር መሳሪያዎቿን የየሞከር ስራዋን አጠናክራ ቀጥላለች።

ሀገሪቱ በርከት ያሉ የአጭር ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎችን ሙከራውን በደቡብ ኮሪያና በጃፓን መካከል በሚገኝ ባህር ላይ መሞከሯን የደቡብ ኮሪያ ጦር አስታውቋል።

በሚሳኤሎቹ ሙከራ ጉዳይ ላይ የደቡብ ኮሪያ ጦር ተጨማሪ ማጣሪያዎችን እያደረገ መሆኑንም አስታውቋል።

የአሜሪካ እና የደቡብ ኮሪያ ጥምር የደህንነት ባለስልጣናትም በሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት ተወንጫፊ ሚሳኤሎች ሙከራ ዙሪያ ተጨማሪ ማጣሪያ እና ምርመራ እየደረጉ መሆኑም ታውቋል።

ምንጭ፦ reuters.com

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.