የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከዞኑ ኅብረተሰብ ጋር ለመወያየት ጉራጌ ዞን ገቡ

By Shambel Mihret

March 25, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከዞኑ ኅብረተሰብ ጋር ለመወያየት ዛሬ ጠዋት ጉራጌ ዞን ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ከዞኑ ኅብረተሰብ  ጋር ለመወያየት ዛሬ ጠዋት ጉራጌ ዞን መግባታቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡