Fana: At a Speed of Life!

የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥል ገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት ለኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ትግበራ እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንደሚቀጥል አስታወቀ።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ ከቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት ዋና ሊቀመንበር ቶኒ ብሌየር ጋር ተወያይተዋል፡፡

ውይይቱ በሁለቱ ተቋማት መካከል ያለው ትብብርና በቀጣይ ለመስራት ባቀዷቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

የቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 (ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን) ስትራቴጂ ከዝግጅት ወቅት ጀምሮ እስከ ማስፈጸም ሂደት በቴክኒክ፣በኢ-ሰርቪስ ትግበራ ላይ ጥናት በማድረግ፣ የማስፈጸም አቅም እንዲሁም የአደረጃጀትና የስራ ሂደትን ለማሻሻል የሚያስችል ድጋፍ ሲያደርግ መቆየቱ ተገልጿል።

ኢንስቲትዩቱ ከዲጂታል መሰረተ ልማት አኳያ በዳታ ማዕከል፣ በኢንተርኔት ተደራሽነት፣ በክላውድና በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ላይ በቀጣይ ሊያደርገው በሚችለው ድጋፍ ውይይት መደረጉ ተመላክቷል።

በሌላ በኩል የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ፕሮግራም ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮዳሄ ዘሚካኤል ለቶኒ ብሌየር የዲጂታል መታወቂያን አገልግሎቶች አስመልክቶ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዳይሬክተሩ ኢንስቲትዩቱ ለአገልግሎቱ የሚያደርገውን ድጋፍ እና ከመሰረተ ልማት ጋር ተያይዞ የሚነሱ ችግሮችን በተመለከተ ገለጻ ማድረጋቸው ተጠቅሷል፡፡

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.