የሀገር ውስጥ ዜና

ወልድያ ዩኒቨርሲቲ በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ

By Shambel Mihret

March 25, 2023

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 16 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ካሰለጠናቸው ተማሪዎች በተጨማሪ በልዩ ልዩ የትምህርት ዘርፎች በድህረ ምረቃ 112 ሰልጣኞችን አስመርቋል።

ዩኒቨርስቲው ከቅዱስ ላሊበላ ቅርስና ጥናት ግቢ 25 ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ በድህረ ምረቃ መርሐ ግብር አስመርቋል።

ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት 160 ሴት አና 430 ወንድ በድምሩ 592 ተማሪዎችን አስመርቋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት አበበ ግርማ  ዩኒቨርሲቲው በወልድያ፣ በመርሳና በላሊበላ ግቢዎች  በጤና፣ በቱሪዝም፣ በግብርናና በቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከላት እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ዩኒቨርሲቲው ከ2004 ዓ •ም   ጀምሮ የምርምርና የልህቀት ሥራ እየሠራ እንደሚገኝ አሚኮ ዘግቧል።