Fana: At a Speed of Life!

የጉራጌ ሕዝብ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው – ጠ/ ሚ ዐቢይ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጉራጌ ሕዝብ የሚነሡ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከጉራጌ ዞን ከተውጣጡ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ የጉራጌ ሕዝብ የሚነሡ ችግሮችን ገንቢ በሆነ ተሳትፎና ውይይት የሚፈታ ሰላም ወዳድ ሕዝብ ነው ብለዋል።

“ዛሬ ባደረግናቸው ውይይቶች ያነሧቸውን ሥጋቶች እና ተስፋዎች በመስማቴ ደስተኛ ነኝ” ሲሉም በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል።

በየደረጃው ሊፈቱ የሚችሉ ችግሮችን ለመፍታት እንሠራለንም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.