Fana: At a Speed of Life!

በካማሺ ዞን ዘላቂ ሠላምን ማረጋገጥ ያለመ ባሕላዊ እርቅ ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካማሺ ዞን ሠዳል ወረዳ አብሮነትን በማጠናከር ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ ያለመ ባህላዊ እርቅ ተካሒዷል።

በስነ ስርዓቱ የካማሺ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብጅጋ ፃፊዮ፣ የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማገሌዎች እንዲሁም አመራሮች እና ነዋሪዎች ተገኝተዋል፡፡

የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ብጅጋ ፃፊዮ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ ሠላሙን በዘላቂነት ለመፍታት እና የቀደመውን አብሮነት ለማጠናከር እርቀ ሠላሙ ትልቅ ፋይዳ አለው፡፡

የሃይማኖት አባቶችና የሃገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው ÷ መንግስት ማህበረሰቡ የሚያነሣቸውን የልማት ጥያቄዎች በወቅቱ ምላሽ ሊሰጥ እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ህብረተሰቡም የልማት ጥያቄዎች ምላሽ እስኪያገኙ በትዕግሥት መጠበቅና ከመንግስት ጎን መቆም ይጠበቅበታል ብለዋል።

በመድረኩ አብሮነትን በማጠናከር እና ሠላምን በማረጋገጥ ለልማት በጋራ መቆም የሚያስችል ቃለ መሃላ መፈጸሙን ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.