Fana: At a Speed of Life!

የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ የሚያስችል ተጨማሪ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊደረግ ነው

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያን የማክሮ ኢኮኖሚ ክፍተት በማጥበብ የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ይበልጥ ለማሳደግ የሚያስችል ተጨማሪ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ሊደረግ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡

የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ እንዳሉት÷በኢትዮጵያ የተጀመረውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠል የሚያስችል ተጨማሪ ማሻሻያ በማስፈለጉ በቀጣይ ቁጥር ሁለት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ለማድረግ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

የኢኮኖሚ ማሻሻያውም የመልሶ ግንባታ ስራን ለማሳለጥና የማክሮ ኢኮኖሚውን ክፍተት በማጥበብ የግሉን ክፍለ ኢኮኖሚ ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያስችል መሆኑን ገልጸዋል።

በሀገር ውስጥና በውጫዊ ምክንያቶች በኢኮኖሚው ላይ የተፈጠረውን ጫና ለመቀነስም የሚረዳ መሆኑን ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

የኢኮኖሚ ጫናውን በመቋቋም የዋጋ ንረትን ለመቆጣጠር፣ የውጭ ምንዛሬ አቅምን ለማሻሻልና ኢንቨስትመንትን ለማሳደግ ቀጣይነት ያለው የፖሊሲ እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።

በሰው ሰራሽና በተፈጥሮ አደጋ ምክንያት በኢኮኖሚው ላይ የተፈጠረውን ጫና መቋቋም የሚያስችል የማሻሻያ ስራ እየተከናወነ ነው ማለታቸውንም ኢዜአ ዘግቧል።

በግብርና ምርቶች ከሀገር ውስጥ ፍጆታ ባለፈ ለውጪ ገበያ የማዋል ጥረቱም የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

ኢትዮጵያ ያለባትን የእዳ ጫና ወደ መካከለኛ ደረጃ እንዲወርድ በማድረግ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደርን ማሻሻል የሚያስችል የፖሊሲ እርምጃ ይወሰዳልም ነው ያሉት፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.