Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኢራንን አስጠነቀቁ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካው ፕሬዚዳንትጆ ባይደን ኢራንን ክፉኛ አስጠንቅቀዋል፡፡

በሰሜን ምስራቅ ሶሪያ በሚገኘው የአሜሪካ ጦር ሰፈር ላይ ዋሺንግተን “ከኢራን ጋር ግንኙነት አላቸው” ባለቻቸው ታጣቂዎች ተደጋጋሚ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙ ተገልጿል፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን ጉዳዩን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ÷ አሜሪካ በቀጣናው የሚስተዋለውን የሽብር ድርጊት ለመመከት የምታደርገውን ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

“ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ታጣቂዎች” አሸባሪዎችን እየተዋጉ በሚገኙ የአሜሪካ ወታደሮች ላይ የፈጸመት ጥቃት ተገቢነት የሌለው ነው ሲሉ ኮንነዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስም ጥቃቱን በፈጸሙ አካላት ላይ አስፈላጊውን አጸፋዊ እርምጃ እንደምትወስድ ነው ያስገነዘቡት፡፡

አሜሪካ ከኢራን ጋር ምንም አይነት ግጭት አትፈልግም ያሉት ፕሬዚዳንቱ ÷በአንጻሩ ኢራን በተንኳሽ ድርጊቷ ቀጥላበታለች ብለዋል፡፡

ስለሆነም አሜሪካ የሕዝቦቿን ደህንነት በሃይል ለማስጠበቅ አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጋለች ነው ያሉት፡፡

በጦር ሰፈሩ ላይ በተፈጸመው ጥቃት አራት የአሜሪካ ወታደሮች ሲቆስሉ ÷ አንድ ወታደር ደግሞ ህይወቱ ማለፉን አርቲ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.