Fana: At a Speed of Life!

በሐረር ከተማ ባለሃብቶችንና ነዋሪዎችን በማሳተፍ የተለያዩ የልማት ሥራዎች መከናወናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 16፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለሃብቶችንና የከተማው ነዋሪዎችን በማሳተፍና ንቅናቄ በመፍጠር የተለያዩ የልማት ሥራዎች መከናዎናቸውን የሐረር ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ፡፡

የማዘጋጃ ቤቱ ሥራ አስኪያጅ ኢስማኢል ዮስፍ÷በከተማዋ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለማዳረስም ተጨማሪ 16 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለው የመንገድ ዳር የመብራት መስመር መዘርጋቱን አንስተዋል።

ከዚህ ባለፈም 3 ነጥብ 96 ኪሎ ሜትር የእግረኛ መንገድ፣10 ሺህ 611 ካሬ ሜትር አረንጓዴ ስፍራዎችን የማስዋብ ሥራ መከናወኑንም አስረድተዋል።

በተለይም በዓለም ቅርስነት የተመዘገበው ጀጎል ግንብ ዙሪያ የተገነቡት የአረንጓዴ ስፍራዎች ቅርሱ በዘላቂነት እንዲጠበቅ ከማመቻቸታቸውም ባለፈ የቱሪስቱን ቆይታ በማራዘም ከዘርፉ የሚገኘውን ገቢ ለማጠናከር አስተዋጽኦ ማድረጉን ገልጸዋል።

በከተማዋ ከደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ጋር በተያያዘ ያሉትን ችግሮች ለማቃለልና በዘርፉ ለዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር ረገድም አበረታች ሥራዎች እንደተከናወኑ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.