Fana: At a Speed of Life!

በምሥራቅ አፍሪካ ከ9 ነጥብ 5 ሚሊየን በላይ የቤት እንስሳት በድርቅ ምክንያት ሞተዋል- ተመድ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና ኬንያ በትንሹ 9 ነጥብ 5 ሚሊየን የቤት እንስሳት በድርቅ ምክንያት መሞታቸውን የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታወቀ።

በአምስት የዝናብ ወቅቶች ዝናብ አለመጣሉን ተከትሎ ተከስቶ የነበረው ድርቅ በቀጣናው የምግብ እና የገቢ ምንጭ በሆነው የእንስሳት ሀብት ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ነው የተባለው፡፡

ይህም የአርብቶ እና አርሶ አደሩን ኑሮ፣ ገቢ እና አመጋገብ እንዳዛባው ተገልጿል።

በሀገራቱ 5 ነጥብ 1 ሚሊየን ያህል ሕጻናት ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውም ተጠቁሟል፡፡

እንዲሁም 3 ነጥብ 6 ሚሊየን ያህል ሕጻናት ትምህርታቸውን የማቋረጥ አደጋ እንደተጋረጠባቸው እና በተለይም ሴቶች ተጋላጭ ስለመሆናቸው ተነስቷል፡፡

የዓለም ምግብ ፕሮግራም በ2023 በድርቅ ለተጎዱ 8 ነጥብ 8 ሚሊየን ዜጎች አስቸኳይ የሕይወት አድን ምግብ ለማሟላት 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልገው ጠቅሶ ሲ ጂ ቲ ኤን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.