Fana: At a Speed of Life!

በአሜሪካ ግዛቶች በተከሰተ አውሎ ንፋስ 26 ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ሚሲሲፒ እና አልባማ ግዛቶች በተከሰተ ከባድ አውሎ ንፋስ 26 ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

ባለፈው አርብ ጀምሮ የተከሰተው ከባድ አውሎ ንፋስ በሚሲሲፒ ግዛት 25 ሰዎችን ለህልፈት ሲዳርግ ከአልባማ ግዛት ደግሞ በአደጋው የአንድ ሰው ህይዎት አልፏል፡፡

አውሎ ንፋሱ በሚሲሲፒ ግዛት የምትገኘዋን ሮሊንግ ፎርክ ከተማ ማውደሙ የተገለፀ ሲሆን ፥ ነፋሱ የከተማዋን ቤቶች ወደ ፍርስራሽነት ቀይሯል ፣መኪናዎችን ገልብጧል  የከተማዋን የውሃ ግንብ ንዷል ነው የተባለው፡፡

በግዛቶቹ የሚገኘው የጃክሰን ብሄራዊ የአየር ሁኔታ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው÷ነፋሱ ከፍተኛ ኃይል ያለው መሆኑን በመግለፅ በሰዓት ከ265 እስከ 320 ኪሎ ሜትር የሚደርስ ኃይል እንዳለው አመላክቷል፡፡

በግዛቶቹ የተከሰተውን ከባድ አውሎ ንፋስ ተከትሎ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የድንገተኛ አደጋ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጃቸውን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.