Fana: At a Speed of Life!

ከንቲባ አዳነች ከመዲናዋ ነዋሪዎች ጋር መከሩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ከነዋሪዎች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡

ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው እንዳስታወቁት ÷ ሊታረሙ በሚገቡ እንዲሁም ትኩረት በሚፈልጉ ጉድለቶቻችን ላይ የመፍትሔ አቅጣጫዎችን አስቀምጠናል ብለዋል።

በውይይቱ ከተማዋን የሚመጥን አስተሳሰብ ማሰረፅ፣ ፅንፈኝነት ፣ ጥላቻንና ህዝብን የሚከፋፍሉ የሴራ ፖለቲካን በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውንም ነው ያነሱት፡፡

በተጨማሪም የኑሮ ውድነት ጫናን መቀነስ ፣ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎችን የሚደግፉ ፕሮጀክቶችን ማስፋፋት እንዲሁም ከህዝቡ የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሰራ አመላክተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.