Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ቻይና በግብርናው ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማደስ ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና ቻይና በግብርናው ዘርፍ ያላቸውን ግንኙነት ለማደስ ተሥማሙ፡፡

አምባሳደር ተፈራ ደርበው በቻይና የግብርና ሚኒስቴር የዓለም አቀፍ አጋርነት ክፍል ኃላፊ ከሆኑት ኒ ሆንግሺንግ እንዲሁም በምዕራብ እስያ እና አፍሪካ ጉዳዮች የዓለም አቀፍ ትብብር ሊዩ ጂያንግ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸው ወቅት ሀገራቱ ቀደም ሲል በግብርናው ዘርፍ የደረሱትን የመግባቢያ ሰነድ አንስተው መክረዋል።

በዚህ ወቅትም ስምምነቱን ወደ ትግበራ መቀየር በሚቻልባቸው አስቻይ ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውም ነው የተመለከተው፡፡

ሁለቱም ወገኖች በመደበኛነት ለመገናኘት እና በግብርናው ዘርፍ ላይ ያላቸውን ትብብር ለመቀጠል ተሥማምተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.