Fana: At a Speed of Life!

የዓለማችን የምጣኔ ሐብት ቀውስ እየተባባሰ መምጣቱ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለማችን የምጣኔ ሐብት ቀውስ እየተባባሰ መምጣቱን የዓለምአቀፉ የገንዘብ ተቋም አስታወቀ፡፡

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክሪስታሊና ጆርጂየቫ ፋይናንሱ “ከድጡ ወደ ማጡ” እየገባ ነው ሲሉ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ማሳሰቢያ የሠጡት ቤጂንግ በተካሄደው የቻይና የልማት ፎረም ላይ ነው፡፡

ሥራ አስፈፃሚዋ በዘንድሮው ዓመት ቻይና ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በድጋሚ በከፈተችው የኢኮኖሚ አካሄድ ምጣኔ ሐብቷ በ5 ነጥብ 2 በመቶ ሊያድግ ይችላል የሚል መላምት “አይ ኤም ኤፍ” ማስቀመጡን ጠቁመዋል፡፡

ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ሁኔታውን በአንክሮ እየተከታተለ እንደሆነ መናገራቸውንም ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

በዓለምአቀፍ ደረጃ ተከስቶ የቆየው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ እና በዩክሬን አሁንም እየተካሄደ የሚገኘው ጦርነት የዓለምአቀፉ ምጣኔ ሐብት ላይ ቀላል የማይባል ተፅዕኖ ማሳደራቸውን በቤጂንጉ ፎረም ላይ አስረድተዋል፡፡

ይህን ተከትሎም በዘንድሮው አመት የዓለም ኢኮኖሚ ከ3 በመቶ በታች እድገት ሊያስመዝግብ ይችላል ነው የተባለው።

ይህም ከዚህ ቀደም ከተመዘገበው ዝቅተኛ የምጣነኔሀብት እድገት አንጻር እጅግ ዝቅተኛ መሆኑን ስራ አስፈጻሚዋ ጠቁመዋል።

ዓለም አቀፍ ባለሐብቶች እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከእንደ ክሬዲት ስዊዝ ፣ ሲልከን ቫሊ እና ከአሜሪካው ቀጣናዊ አበዳሪ ሲግኔቸር ባንክ በፈለጉት መጠን የብድር አቅርቦት ማግኘት ባለመቻላቸው የባንኩ ዘርፍ ላይ ያላቸው አመኔታ ጥያቄ ውስጥ መውደቁም ተነግሯል፡፡

የግሉ ዘርፍ እና የመንግስት ኢንተርፕራይዞች የሚያፈሷቸው መዋዕለ-ንዋይ የትምህርቱን ዘርፍ ታሳቢ ያደረገ መሆን እንዳለበትም አስገንዝበዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.