Fana: At a Speed of Life!

“የፒያኖዋ እመቤት” እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ አረፉ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የፒያኖዋ እመቤት” እማሆይ ፅጌማርያም ገብሩ አረፉ።
 
እማሆይ ፅጌማርያም በኢትዮጵያ ቀዳሚዋ የቫዮሊን እና ፒያኖ አቀናባሪ እንደነበሩ ይነገራል።
 
እማሆይ ፅጌማርያም ከአባታቸው ከአቶ ገብሩ ደስታ እና እናታቸው ወይዘሮ ካሣዬ የለምቱ በ1916 ዓ.ም በአዲስ አበባ ውስጥ ነው የተወለዱት።
 
በልጅነታቸው ለትምህርት በሄዱባት ስዊዘርላንድ ፒያኖን በደንብ ተምረዋል።
 
ከትምህርት መልስም በ19 አመታቸው ነበር ወደ ወሎ ግሸን ማርያም ገዳም በመሄድ በ21 አመታቸው ምንኩስናን የተቀበሉት።
 
ወላጆቻቸው ያወጡላቸው ስም የውብዳር ሲሆን በወጣትነታቸው ምንኩስናን ከተቀበሉ በኋላ መጠሪያቸው ወደ እማሆይ ፅጌማርያም ተቀይሯል።
 
ከ19 84 ዓ.ም ጀምሮ ኑሯቸውን በክርስትና ሃይማኖት ተከታዮች ዘንድ “ቅድስቲቷ ከተማ” ተብላ በምትጠራው እየሩሳሌም አድርገዋል።
 
አባታቸው ገብሩ ደስታ የአዲስ አበባ ከንቲባ የነበሩ ሲሆን በአፄ ሃይለስላሴ ዘመንም የፓርላማ አፈ ጉባኤ በመሆን ማገልገላቸውን የቤተሰባቸው ታሪክ ያስረዳል።
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.