ስፓርት

ቀሪ የሊጉ ጨዋታዎች ከመጋቢት 23 ቀን ጀምሮ ይካሄዳሉ

By Mikias Ayele

March 27, 2023

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤትኪንግ ኢትዮጵያ ፕሪሚየርሊግ ቀሪ ጨዋታዎች ከመጋቢት 23 ቀን ጀምሮ በአዳማ ከተማ መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ፡፡

አክሲዮን ማህበሩ የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 ውድድር ቀጣይ መርሐ ግብር የሚጀምርበትን ቀን ለክለቦች ይፋ አድርጓል።

በዚህም መሰረት ከ17ኛ እስከ 27ኛ ሳምንት ያሉ ጨዋታዎች በአዳማ ከተማ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እና በሐዋሳ ከተማ ሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም የሚካሄዱ ይሆኗል፡፡

የውድድሩ ሙሉ መርሐ ግብር በቅርቡ ለክለቦች የሚገለፅ መሆኑን ከቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡