ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ከተመድ የአከባቢ ጥበቃ ረዳት ሴክሬተሪ ጀኔራል ኤልሳቤት ሜሪማ ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአከባቢ ጥበቃ ረዳት ሴክሬተሪ ጀኔራል ኤልሳቤት ሜሪማ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ በአከባቢ ጥበቃ ችግሮች እና የመፍትሄ ሃሳቦች ዙሪያ መክረዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ፣ ናይሮቢ በነበሩበት ወቅት ሴቶች ለከፍተኛ የአመራርነት ቦታ እንዲበቁ በርካታ የማብቃት ሥራዎችን እንደሠሩ አስታውሰዋል፡፡
ሜሪማም ለዚህ ከፍተኛ የሃላፊነት ደረጃ በመሾማቸው የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክትም ማስተላለፋቸውን ከፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡