Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ የሚመረቱ ምርቶች በናይጄሪያ ገበያ እንዲያገኙ ለማስቻል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች በናይጄሪያ ገበያ እንዲያገኙ ለማስቻል ውይይት ተካሂዷል፡፡

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በኢትዮጵያ ከናይጄሪያ አምባሳደር ቪክቶር አዴሌክ ጋር በኢንቨስትመንት ተኮር ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

አቶ አክሊሉ ታደሰ በውይይቱ ወቅት÷ ናይጄሪያ በርካታ ህዝብ እንዳላት ጠቅሰው ይህም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ የሚመረቱ ምርቶች ሰፊ የገበያ አማራጮች እንዲያገኙ ትልቅ እድል እንደሚፈጥር ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም በናይጄሪያ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ባለሀብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው ማምረት እንዲችሉ ኮርፖሬሽኑ ያስቀመጣቸውን ምቹ ሁኔታዎችና ማበረታቻዎች ለአምባሳደሩ አስረድተዋል።

አምባሳደር ቪክቶር በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ያከናወነችው የሪፎርም ስራዎች ትኩረት የሚስቡ መሆናቸውና ባለሃብቶችን የሚያነቃቃ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በኢንቨስትመንት ትስስር ጉዳይ በጋራ መስራት እንደሚያስፈልግ መግለጻቸውንም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.