Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ተቋም ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም አቀፉ የፀረ-አበረታች ቅመሞች ተቋም ፕሬዚዳንት ዊቶልድ ባንካ ጋር ተወያዩ።

ሚኒስትሩ ስፖርት የዲፕሎማሲ አንዱ መሳሪያ እንደሆነ በመግለጽ በሀገራት መካከል ትብብር ለመፍጠር የሚያስችል መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

አበረታች ቅመሞች በስፖርት ላይ ያላቸውን ተፅዕኖ ለመከላከልና ለመቆጣጠር መንግስት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተባብሮ እንደሚሰራም በዚህ ወቅት ተናግረዋል።

ዊቶልድ ባንካ በበኩላቸው የኢትዮጵያ መንግስት አበረታች ቅመሞች መጠቀምን ለመከላከል ለሚያደርገው ጥረት ያላቸውን አድናቆት ገልዋል።

አያይዘውም ተቋሙ ሀገራዊ እና ተቋማዊ አቅምን ለማጠናከር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አስረድተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.