Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያን በግብርናው ዘርፍ ተመራጭ  ለማድረግ በጋራ መሥራት እንደሚገባ ተመለከተ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 18 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ በግብርናው ዘርፍ ተመራጭ ሀገር እንድትሆን በጋራ መስራት ይገባል ሲሉ የፈረንሳይ የምስራቅ አፍሪካ እና የህንድ ውቅያኖስ የግብርና አማካሪ ቪንሰንት አብቲ ተናገሩ፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚንስትር  በለጠ ሞላ ከፈረንሳይ መንግስት የምስራቅ አፍሪካ እና የህንድ ውቅያኖስ አካባቢ የግብርና እና የምግብ አማካሪ ቪንሰንት አብቲ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ሚኒስትሩ በውይይቱ ላይ እንዳሉት÷ ግብርናን በቴክኖሎጂ ለማገዝ እንደ ፈረንሳይ ካሉ ሀገራት ልምድ በመውሰድ ሊሰራ ይገባል፡፡

የአርሶአደሩን  የባለቤትነትና የምርት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥም መንግስት እየሠራ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያን ምርቶች በዓለም አቀፍ ደረጃ በማስተዋወቅ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ከፈረንሳይ መንግስት ጋር በትብብር መስራት አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

ቪንሰንት አብቲ ÷ ኢትዮጵያ ያላትን የግብርና ምርት ለዓለም ገበያ እንድታቀርብ  የፈረንሳይ መንግስት በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

የኢትዮጵያን ተጠቃሚነት ከሚያረጋግጡት አንዱ ÷ ኢኖቬቲቭ ግብርናን በመጠቀም የግብርና ምርቶችን  አካባቢያዊና አዕምሯዊ ጥበቃ ኖሯቸው ወደ ዓለም ገበያ ማቅረብ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡

በቀጣይ የሁለትዮሽ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጡ የጋራ አሰራሮች ተቀርጸው ወደ ትግበራ መግባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለመመምከር ስምምነት ላይ መደረሱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.