Fana: At a Speed of Life!

ከ42 ሺህ ኩንታል በላይ የግብርና ምርት ወደ መዲናዋ ገብቷል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዛሬው ዕለት ከኦሮሚያ ክልል ከ42 ሺህ ኩንታል በላይ የግብርና ምርቶች ወደ አዲስ አበባ መግባታቸውን የከተማዋ ንግድ ቢሮ አስታወቀ፡፡

የኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አወሉ አብዲ ምርቶቹን ለመዲናዋ የሥራ ኃላፊዎች ማስረከባቸውም ተገልጿል፡፡

በርክክቡ ወቅት አቶ አወሉ ባደረጉት ንግግር በቅርቡ ከ40 እስከ 50 ሺህ ኩንታል ልዩ ልዩ አስፈላጊ የግብርና ምርቶች በቀጣይ ቀናት ወደ አዲስ አበባ ከተማ ይገባሉ ብለዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከክልሎች ጋር እያደረገ ባለው የገበያ ትስስር መሰረት ከኦሮሚያ ክልል እያስገባ ያለው የግብርና ምርት መቀጠሉንም ነው ቢሮው ያስታወቀው፡፡

ዚህ ቀደም ከ28 ሺህ በላይ ልዩ ልዩ የግብርና ምርት ወደ መዲናዋ ገብቶ ለህብረተሰቡ መከፋፈሉንም አስታውሰዋል፡፡

በከተማው የሚስተዋለው ፍላጎት ከፍተኛ በመሆኑ ከ219 በላይ በኦሮሚያ የሚገኙ ወፍጮ ቤቶች÷ የበቆሎ፣ የስንዴና የጤፍ ዱቄት ለከተማው ህብረተሰብ እያቀረቡ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

በቅርቡ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በክልሉ የተመረተ የበጋ ስንዴ ወደ ገበያ እንዲገባ ቅድመ ዝግጅ እየተደረገ መሆኑንም ነው አቶ አወሉ የገለጹት፡፡

ገበያውን ለማረጋጋት የሚያስችል በቂ የምግብ ምርት በሀገር አቀፍ ደረጃ መኖሩንም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

መንግስት የየግብርና ምርቶችን በመሰወርና አላስፈላጊ በሆነ መልኩ ዋጋ በመጨመር የፖለቲካ መሳሪያ በሚያደርጉ አካላት ላይ አስፈላጊውን ሁሉ እርምጃ ይወስዳል ማለታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ከተማ አስተዳደሩ ከክልሎች ጋር በሚያደርገው የገበያ ትስስር የግብርና ምርቶች በሚፈለገው ደረጃ በስፋት እንዲገቡ እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት የዋጋ ንረቱን በዘላቂነት ማርገብ እንደሚቻልም አመላክተዋል፡፡

ህብረተሰቡ የግብርና ምርቶችን የመሰወር እንቅስቃሴዎች ሲመለከት መረጃ በመስጠት ከከተማ አስተዳደሩ ጋር ለህግ መከበር እንዲሰራ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ሕዝብና መንግስት ላደረጉት ትብብር ያመሰገኑት አቶ ጃንጥራር÷ በዘላቂነት ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.