Fana: At a Speed of Life!

ዘመናዊ የጤና መረጃ አያያዝና አጠቃቀም ተግባራዊ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሀገር አቀፍ ደረጃ ዘመናዊ የጤና ዘርፍ የመረጃ አያያዝና አጠቃቀም ተግባራዊ በማድረግ ለታካሚው የተሻለ አገልግሎት ለመሥጠት እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

“የግሉን የጤና ዘርፍ ተሳትፎ፣ ዐቅምና ተጠያቂነት እናጠናክር” በሚል መሪ ቃል ሀገር አቀፍ የጤና መረጃ ሣምንት እየተከበረ ነው።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ደረጄ ዱጉማ የመረጃ ጥራት በጤናው ዘርፍ የወጡ ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞችን ለማሻሻልና ኅብረተሰቡን የሚጠቅሙ አዳዲስ ፕሮግራሞችን ለመቅረጽ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የጤና መረጃ ሥርዓት መዘመኑ በሕክምናው ዘርፍ የሚያጋጥሙ የሕክምና ስህተቶችን አጣርቶ ትክክለኛ ውሳኔ እንዲያገኙ ለማድረግና በዘርፉ የሚስተዋሉ የንግድ ማጭበርበሮችን ለመከላከል ይጠቅማል ብለዋል፡፡

ጥራቱና ደኅንነቱ የተረጋገጥ መድኃኒት በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ እና ተገቢውን የሕክምና ምክረ-ሐሳብ ለኅብረተሰቡ ለማድረስ የመረጃ አያያዝን ማዘመን አስፈላጊ እንደሆነም አክለዋል፡፡

ከግል የጤና ተቋማት እንዲሁም ከሌሎችም ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ዘመናዊ የጤና መረጃ አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት ላይ መሆኑንም ጠቁመዋል።

የጤና መረጃ ሣምንት የጤና ሚኒስቴርን ጨምሮ በተዋረድ እስከ ጤና ተቋማት ድረስ የጤና መረጃ ጥራት ተደራሽነትንና አጠቃቀምን ለማሳደግ ዓላማ ይዞ በተለያዩ መርሐ-ግብሮች መከበር ጀምሯል።

በዓሉም ከዛሬ ጀምሮ እስከ መጋቢት 22 በተለያዩ መርሐ-ግብሮች በሁሉም የጤና ተቋማት ይከበራል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.