Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ለመስኖ ልማት የሚውል 23 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ የከርሰ-ምድር ውኃ እንዳላት ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ለመስኖ ልማት ከ30 ሜትር ባነስ ጥልቀት ላይ የሚገኝ 23 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ የከርሰ-ምድር የውኃ ሃብት እንዳላት መረጋገጡን የግብርና ትራንስፎርሜሽን ኢንስቲትዩት ገለጸ።

የኢንስቲትዩቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ማንደፍሮ ንጉሤ እንደገለጹት÷ ከዝናብ ጠባቂነት የተላቀቀ የግብርና ክፍለ ኢኮኖሚ ለመገንባት እየተሰራ ነው፡፡

በዚህም ዝናብ ጠብቆ በዓመት አንድ ጊዜ ከማምረት ባሻገር በመስኖ ልማት በዓመት እስከ ሦስት ጊዜ የማምረት እንቅስቃሴ ውስጥ መገባቱንም ጠቅሰዋል።

ለመስኖ ልማት ዕቅድ መሳካት ትልቅ ሚና እየተጫወተ ካለው የገፀ-ምድር ውሃ ባሻገር በሀገሪቱ ከ30 ሜትር ባነሰ ጥልቀት የከርሰ-ምድር የውኃ አቅም መለየቱን ነው የገለጹት፡፡

በዚህም÷ በአነስተኛ ጥልቀት ተቆፍሮ ጥቅም ላይ ሊውል የሚችል 23 ቢሊየን ሜትር ኪዩብ የከርሰ-ምድር ውኃ አቅም መኖሩ መረጋገጡን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በገፀ-ምድርና አሁን በተረጋገጠው ጥልቅ ያልሆነ የከርሰ-ምድር ውኃ እስከ 6 ሚሊየን ሄክታር ማልማት እንደሚቻል ጠቁመው፤ በረዥም ጊዜ ውስጥ የውኃ ኃብትን በአግባቡ በመጠቀም እስከ 11 ሚሊየን ሄክታር በመስኖ የማልማት አቅም እንዳለ ተናግረዋል።

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.