Fana: At a Speed of Life!

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ካቢኔ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል።

ካቢኔው ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የመንግስትን የሠላም አማራጭ ተቀብለው የተመለሱ ዜጎች የልማት እና የኢኮኖሚ ተጠቃሚ በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት ተወያይቶ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡

በሁሉም የክልሉ ዞኖች የሚገኙ የሠላም ተመላሾች በግብርና፣ በማዕድን፣ በንግድ እና ሌሎች ዘርፎች ተሠማርተው ወደሥራ እንዲገቡ ለማስቻል ተጨማሪ የትራክተተር፣የማዕድን ማውጫ ማሽነሪ፣ የመነሻ ካፒታል ድጋፍን ጨምሮ የተለያዩ ምቹ ሁኔታዎች እንዲፈጠሩም ወስኗል፡፡

በተጨማሪም ካቢኔው የዝግጅት ሥራዎች ተጠናቀው የሠላም ተመላሽ ዜጎች በአጭር ጊዜ ወደሥራ እንዲገቡና የኢኮኖሚ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ውሳኔ ማሳለፉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን  መረጃ ያመላክታል፡፡

የክልሉ ካቢኔ ቀደም ሲል በተለይም የሠላም ተመላሾችን ለማቋቋም ልዩ መመሪያ አውጥቶ ወደ ሥራ መግባቱ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.