Fana: At a Speed of Life!

የኦሮሚያ ክልል በጅግጅጋ ከተማ ያስገነባው ዘመናዊ ትምህርት ቤት ተመረቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 19፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌና የኦሮሚያ ክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች በጅግጅጋ ከተማ የኦሮሚያ ክልል ያስገነባውን “ካህ” የተባለ የሁለተኛ ደረጃ ትምህር ቤት መርቀው ከፈቱ፡፡

የሶማሌ ክልል ርእሰ መስተዳድ ሙስጠፌ መሃመድ በዚሁ ወቅት÷ትምህርት ቤቱ ከፍተኛ የህዝብ ብዛት ባለበት አከባቢ በመገንባቱ ረጅም ታሪካዊ ግንኙነት ያላቸው የሶማሌና የኦሮሞ ወንድማማች ህዝቦች ትብብር፣ትስስርና ግንኙነትን ይበልጥ ያጠናክራል ብለዋል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው÷ትምህርት ቤቱ በኦሮሚያ ክልል ተገንብቶ ለሶማሌ ክልል ህዝብ የተበረከተ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

በተጨማሪም የሁለቱን ክልሎች ወንድማማች ህዝቦች በእውቀት ለማስተሳሰር እና የሁለቱ ክልሎች ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚያግዝም መናገራቸውን ከሶማሌ ክልል ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የተመራ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ልዑክ ጅግጅጋ ከተማ መግባቱ ይታወሳል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.