Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ጃፓን በሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማሙ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 19 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና ጃፓን በሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

ስምምነቱን በግብርና ሚኒስቴር የእርሻና ሆርቲካልቸር ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ መለሰ መኮንን(ዶ/ር) እና የጃፓን ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ተወካይ ሞሪሃራ ካሱኪ ተፈራርመዋል፡፡

የአነስተኛ አርሶ አደሮች የሆርቲካልቸር አቅም ማጎልበቻ ፕሮጀክት በምዕራፍ አንድ ፕሮግራሙ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ላይ ሲሰራ መቆየቱ ተገልጿል፡፡

በምዕራፍ ሁለት መርሐ ግብሩም በደቡብ እና ሲዳማ ክልሎች ላይ ለመስራት በዛሬው ዕለት ውል መፈረሙ ን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ዶ/ር መለሰ መኮንን ÷የጃፓን መንግስት ሆርቲካልቸር ልማት ላይ ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ለመስራት ያለውን ፍላጎት አድንቀዋል፡፡

ሞሪሃራ ካሱኪ በበኩላቸው÷ ፕሮጀክቱ ለአነስተኛ አርሶ አደሮች በሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.