Fana: At a Speed of Life!

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በቅርቡ ግንባታው የተጀመረው የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ የሲቪልና የኤሌክትሮ መካኒካል ስራው በጥሩ አፈጻጸም ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ ግንባታ ሒደትን ጎብኝተዋል።

ፋብሪካው በሰኔ ወር ሙሉ በሙሉ የማሽን ተከላው ተጠናቆ በቀጣዩ ዓመት ጥር ወር ላይ የመጀመሪያ ዙር ምርት ያመርታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተጠቁሟል፡፡

በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባም በቀን 150 ሺህ ኩንታል ሲሚንቶ እንደሚያመርት ነው የተገለጸው።

የግንባታው ዘርፍ ለሀገሪቱ ጥቅል ምርት 19 በመቶ ድርሻ አለው ያሉት ሚኒስትሯ÷ ፋብሪካው በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሲገባ በዘርፉ ያለውን ችግር ይቀርፋል ብለዋል፡፡

ለዚህም መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የለሚ ናሽናል ሲሚንቶ ፋብሪካ በሙሉ አቅሙ ምርት ማምረት ሲጀምር የሀገሪቱን የሲሚንቶ ፍላጎት 50 በመቶ እንደሚሸፍን ተመላክቷል፡፡

በወንድሙ አዱኛ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.