Fana: At a Speed of Life!

“ሠላም ለንግድ ፣ ንግድ ለሠላም” በሚል መሪ ሐሳብ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የዓለምአቀፉ የግል ኢንተርፕራይዞች ማዕከል “ሠላም ለንግድ፣ ንግድ ለሠላም” በሚል መሪ ሐሳብ ውይይት አካሄደ፡፡

በሠላም ሚኒስቴር የሠላም ግንባታና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደአ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ ሠላም በሀገር ውስጥ መዋዕለ-ንዋይ ለማፍሰስ እና ለንግዱ ማኅበረሰብ ውጤታማነት መሠረታዊ ጉዳይ ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስቴሩ ብሔራዊ ምክክር ኮሚሽንን ጨምሮ ከበርካታ ባለድርሻ አካላትና ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በብሔራዊ መግባባትና ሠላም ግንባታ ላይ ተቀናጅቶ እየሠራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በመድረኩ የንግድ ተቋማትና ማኅበረሰብ ተወካዮች በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፉ ላይ እየገጠማቸው ያለውን ፈተናና ቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች የሚያሳይ ሪፖርት አቅርበዋል፡፡

የትግራይ፣ አፋር፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና የአማራ ክልሎች የንግድ ተቋማትና የንግድ ማኅበረሰብ ተወካዮች በመድረኩ ተሳትፈዋል፡፡

የብሔራዊ ምክክር ኮሚሽንም በውይይቱ አንዱ ተሳታፊ እንደነበረ ከሠላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.