Fana: At a Speed of Life!

ለጤናማ ህይወት ጠቃሚ ምክሮች

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ጤና ድርጅት ትርጓሜ መሰረት ጤናማ ህይወት መኖር ማለት በጠና የመታመም ወይም ቀደም ብሎ የመሞት አደጋን የሚቀንስ የአኗኗር ዘይቤ ነው፡፡

ጤናማ የአኗኗር ልማዶችን የዕለት ተዕለት ህይወታችን አካል ካደረግን አደገኛ የሚባሉትን እንደ ስኳር በሽታ፣ የልብ ሕመም እንዲሁም በካንሰር የመታመም አጋጣሚ አነስተኛ እንደሚሆን ነው የዘርፉ ባለሙያዎች የሚናገሩት፡፡

ያም ሆኖ ግን ጤናማ የአኗኗር ዘይቤ ለመኖር የማያቋርጥ እና ተደጋጋሚ ጥረት የሚጠይቅ ነገር እንጅ አንድ ጊዜ ተሰርቶ የሚያልቅ እንዳልሆነ ነው ባለሙያዎች የሚያስረዱት፡፡

ከታች የተጠቀሱት ነጥቦች ደግሞ ጤናማ ህይወት ለመኖር ያግዛሉ ተብለው በዘርፉ ባለሙያዎች የተጠቀሱ ናቸው

1.የተመጣጠነ ምግብ መመገብ ፦ በዕለት ተዕለት ገበታዎ ላይ አትክልት ፣ፍራፍሬ፣ ጥርጥሬ እና ሌሎች የተለያዩ አይነት ያላቸው ምግቦችን ማካተት፣ የጨው እና ስኳር አጠቃቀምን መቀነ እንዲሁም ቅባት የበዛባቸውና ስብነት ያላቸው ምግቦችን ከመመገብ መቆጠብ ያስፈልጋል፡፡

2. በቂ ውሃ መጠጣት ፦ በቀን እስከ 8 ብርጭቆ ውሃ መጠጣትእና ስኳር የበዛባቸውን ጣፋጭ መጠጦችን አለማዘውተር ይመከራል፡፡

3.በየጊዜው ክብደትን መለካት ፦ ክብደትን በየጊዜው መለካት ምን ያህል ክብደት እንደጨመሩ እና ምን ያህል እንደቀነሱ ለማወቅ ስለሚረዳ ጤንነትዎን ለመጠበቅ ይረዳል፡፡

4. በመቀመጥ የሚያሳልፉትን ጊዜ መቀነስ ፦ለረዥም ጊዜ ቴሌቪዥን በመመልከት ወይም ኮምፒውተር ላይ አተኩሮ መቆየት ጤናማ ህይዎትን ከሚጎዱ የአኗኗር ዘይቤዎች ይመደባል።

በቀን ውስጥ ቢያንስ በየ80 ደቂቃው ከመቀመጫው ተበመነሳት ጥቂት መንጠራራትና ባሉበት ቦታ ማፍታት ከተቻለም ቢሮ ኮሪደር ላይ ትንሽ መንቀሳቀስ።

5. የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማዘውተር፦ አንድ ጤናማ ሰው በሳምንት ቢያንስ ለ150 ደቂቃ ያክል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ሊያደርግ ይገባል፡፡

6 የእጅ ንጽህናን በየቀጊዜ መጠበቅ፦ እጅን በሳሙና እና በውሃ ቶሎ ቶሎ መታጠብ ወይንም ሳኒታይዘር በመጠቀም ከባክቴሪያ የጸዳ ማድረግ በርካታ ኢንፌክሽኖችን ለመከላከል ይረዳል፡፡

ይህን ሲመገቡ ብቻ ሳይሆን በማንኛውም ጊዜ ቢያደርጉት ይመከራል፤ በአጋጣሚ ፊትዎን፣ አይንዎን፣ አፍንጫዎን እና ሌላም የሰውነት ክፍልዎን መንካትዎ ስለማይቀር ያን ማድረጉ ለጤናዎ ጠቃሚ ነው።

7.በቂ እንቅልፍ መተኛት ፦ በቂ እንቅልፍ መተኛት ከሰውነት በሽታ የመቋቋምና የመከላከል ችሎታ ጋር ከፍተኛ ቁርኝት አለው ይላሉ የዘርፉ ባለሙያዎች፡፡

በቀን ውስጥ ከ7 እስከ 9 ሰአት መተኛት ለአካላዊም ሆነ አዕምሯዊ ጤንነት ወሳኝ ነው፡፡

8. አልኮል መቀነስ፦ ከመጠን በላይ አልኮል የሚጠጣ ሰው በረጅም ጊዜ ሂደት ለጉበት እና ለጉበት ካንሰር የመጋለጥ እድሉ ሰፊ ነው፡፡

ስለዚህም ከዚህ በመራቅ ጤንነትዎን ይጠብቁ።

9. ጭንቀትን ማስወገድ ፦ጭንቀት ከማይግሪን እስከ ልብ ችግር ለሚደርሱ ከባድ ህመሞች ያጋልጣል፡፡

ስለሆነም ጭንቀት ሲሰማዎት የተለያዩ ዘና የሚያደርጉ እንደ ሙዚቃ ፣ኮሜዲ ፊልሞችን ማየት እና ሌሎች ጭንቀት ማስወገጃ ዘዴዎችን መጠቀም ይልመዱ።

10.ሲጋራ ከማጨስ መቆጠብ፦ ሲጋራ ማጨስ ለሳምባ ካንሰር ዋነኛው መንስኤ ሲሆን ከሳምባ ካንሰር በተጨማሪም ለሌሎች የካንሰር ህመሞች እድገት የራሱን አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ እንዲሁም ለልብ ህመም እንደሚያጋልጥ የዘርፉ ባለሙያዎች ይገልጻሉ፡፡

ሲጋራ የአጫሱን ብቻ ሳይሆን አጠገቡ ያለውን ሰውም ጤና የሚጎዳ በመሆኑ ሲጋራን ከማጨስ መቆጠብ ይገባል፡፡

ምንጭ፥ ኸልዝ ላይን

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.