የሀገር ውስጥ ዜና

አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከሙሳ ፋኪ መሃማት ጋር ተወያዩ

By Mikias Ayele

March 29, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽነር አምባሳደር ተሾመ ቶጋ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሃማት ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደሩ በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት ÷ ከሙሳ ፋኪ መሃማት ጋር በነበራቸው ውይይት የብሄራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ስራዎች አተገባበርን በተመለከት ምክክር አድርገዋል፡፡

ሊቀመንበሩ በኢትዮጵያ  የብሄራዊ ተሃድሶ ስራዎች እንዲሳኩ የአፍሪካ ህብረት ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ እንደሆነ ሊቀ መንበሩ መግለጻቸውንም አስታውቀዋል።

ይህም ለአፍሪካዊ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ በሚለው መርህ የተቃኘ መሆኑን ጠቁመዋል።