Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክለቦች እስከ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ሪፖርት እንዲያቀርቡ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ክልል ክለቦች እስከ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ አጠቃላይ ሪፖርት እንዲያቀርቡ የክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጠይቋል፡፡

በክልሉ በነበረው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ ምክንያት ከውድድር ርቀው የቆዩት የትግራይ ክለቦች ባለፈው እሁድ ከክልሉ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጋር ምክክር አድርገዋል፡፡

በምክክሩም ክለቦቹ ወደ እንቅስቃሴ ስለሚመለሱበት ሁኔታ ውይይት መደረጉን ሶከር ኢትዮጵያ ዘግቧል፡፡

በወቅቱ በክለቦቹ የቀረበው ሪፖርት በቂ ሆኖ ባለመገኘቱ እስከ ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም ሪፖርታቸውን አጠቃለው እንዲያስረክቡ የክልሉ እግር ኳስ ፌደሬሽን የጊዜ ገደብ አስቀምጧል፡፡

በሌላ በኩል ፌደሬሽኑ ዛሬ ዘጠኝ አባላት ያሉት የክልሉን እግርኳስ ቀጣይ እርምጃ የሚያጠና የቴክኒክ ኮሚቴ እንደሚያቋቁም ተሰምቷል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.