የሀገር ውስጥ ዜና

ሚኒስቴሩ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰበውን ድጋፍ አስረከበ

By ዮሐንስ ደርበው

March 29, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በኦሮሚያ ክልል በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ያሰባሰበውን 8 ሚሊየን 45 ሺህ ብር ለክልሉ መንግሥት አስረከበ፡፡

ሚኒስቴሩ በኦሮሚያ ክልል ቦረና፣ ባሌ፣ ጉጂ፣ አርሲ እና ሐረርጌ አካባቢዎች ያጋጠመውን የድርቅ አደጋ ለመመከት እንዲቻል የንግዱን ማህበረሰብ በማስተባበር ያሰባሰበውን ገንዘብ ነው ዛሬ ያስረከበው፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግስትም ለተደረገው ድጋፍ የምስጋና የምስክር ወረቀት ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አበርክቷል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!