Fana: At a Speed of Life!

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ከዓለም አቀፍ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የዓለም አቀፍ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ፕሬዚዳንት ዊቶልድ ቦንካ እና የልዑካን ቡድናቸውን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፍ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲ ይበልጥ ተቀራርበው በፀረ-አበረታች ቅመሞች ቁጥጥር እና ምርመራ ላይ ሊሠሩ ስለሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በተጨማሪም ድርጅቱ የተለያዩ ድጋፎችን በሚያደርግበት ላይ ተወያይተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአትሌቲክስ ስፖርት የረጅም ጊዜ ታሪክ ያላት እና አትሌት አበበ ቢቂላ በሮም ማራቶን ድል ካደረገ ጊዜ ጀምሮ በዓለም መድረክ የታወቀች መሆኗን ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ አስረድተዋል፡፡

ድርጅቱ በፀረ-አበረታች ቅመሞች ቁጥጥር ላይ ለሚያደርጋቸው የቴክኒክ ድጋፎች ምስጋና ማቅረባቸውንም ከፕሬዚዳንት ጽሕት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.