Fana: At a Speed of Life!

በአፋር ክልል 2 ሺህ በሚጠጉ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፋር ክልል ንግድ፣ ገበያ ልማትና ኢንዱስትሪ ቢሮ ባደረገው የክትትልና ቁጥጥር ስራ ሕግን ተላልፈዋል ባላቸው 1 ሺህ 986 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ፡፡

ቢሮው ለሕብረተሰቡ ምርት በማቅረብ እንዲሁም ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ረገድ በትኩረት እየሠራ መሆኑን ገልጿል፡፡

በቢሮው ፍትሐዊ የንግድ ክትትልና ቁጥጥር የገበያ ልማት ዳይሬክተር አብዱ አሊ÷ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለሕብረተሰቡ እየቀረቡ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

በሌላ በኩል ቢሮው ባስቀመጠው ዋጋ በማይሸጡ ነጋዴዎች ላይ በንግድ ምዝገባና ፈቃድ አዋጅ ቁጥር 980/2008 መሰረት ሕጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል፡፡

በዚሁ መሰረት በሁለት ወር ውስጥ በአምስት ከተሞች እና ስምንት ወረዳዎች በ4 ሺህ 80 የንግድ ተቋማት ላይ የክትትልና ቁጥጥር ሥራ ተከናውኖ 1 ሺህ 986 ጥፋተኛ ሆነው ተገኝተዋል ነው ያሉት፡፡

እደጥፋታቸው ደረጃም የቃል ማስጠንቀቂያ፣ የጽሑፍ ማስጠንቀቂያ፣ አገልግሎት እንዳይሰጡ ማሸግ፣ የንግድ ፈቃድ ማገድ ብሎም የመሠረዝ እርምጃ መወሰዱን አስረድተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.