Fana: At a Speed of Life!

የያቤሎ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያና ማስተላለፊያ መስመር ሥራ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 6፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት በቦረና ዞን ያቤሎ ወረዳ የተገነባው የያቤሎ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና ማስተላለፊያ መስመር ሥራ ጀመረ።

የባለ 132 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ እና ማስተላለፊያ መስመር የሆነው ፕሮጀክት የፍተሻ እና ሙከራ ሥራ ተጠናቆ በዛሬው ዕለት ኃይል መስጠት ጀምሯል ነው የተባለው።

ጣቢያው በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መካከል በተደረገ የኮንትራት ሥምምነት  የተገነባ  ነው ተብሏል።

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው 132 ኪሎ ቮልት ኃይል የመሸከም አቅም ያለው ሲሆን፥ አንድ ባለ 20/25 ሜጋ ቮልት አምፔር ትራንስፎርመርም ተተክሎለታል።

በማከፋፈያ ጣቢያው የመቆጣጠሪያ ክፍሎች፣ የመኖሪያ ቤቶች እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶች ግንባታም ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉም ተገልጿል።

የፕሮጀክቱ መገንባት በያቤሎ ከተማ እና አቅራቢዋ ባሉ አካባቢዎች ይስተዋል የነበረውን የኃይል አቅርቦት ችግር ይፈታል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ገፃችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ!

https://t.me/fanatelevision

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.