Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ለውሃ እቀባና አሰባሰብ ስራ የተለየ ትኩረት እንደሚሰጥ ገለጸ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 20 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ለውሃ እቀባ እና አሰባሰብ ስራዎች የተለየ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚሰራ አስታወቀ፡፡

የዝናብ ውሃን በማቀብ የበልግ ግብርናን ለማሳካት፣ ለእንስሳት እርባታ፣ ለፍራፍሬና ለጓሮ አትክልት ልማት ማዋል እንደሚገባ በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪና የደቡብ ክልል ግብርና ቢሮ ኃላፊ ኡስማን ሱሩር ተናግረዋል፡፡

የበልጉን አዝመራ ውጤታማ ለማድረግ ሁሉንም የእርጥበት አማራጮች አሟጦ መጠቀም እንደሚያስፈልግም አሳስበዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት እየጣለ ያለውን ዝናብ በመጠቀም የደራሼ ልዩ ወረዳ አርሶ አደሮች የተለያዩ የውሃ አሰባሰብ ዘዴዎችን በመጠቀም እያደረጉት ያለውን ጥረት አድነቀዋል፡፡

የውሃ እቀባ ስራው በሌሎች አካባቢዎችም ሊለመድ ይገባል ማለታቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.