Fana: At a Speed of Life!

33 ኢትዮጵያውያን ከፑንትላንድ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015(ኤፍ ቢ ሲ) 33 ኢትዮጵያውያን ከፑንትላንድ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተገለጸ፡፡

በፑንትላንድ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ቆንስላ ጄነራል ጽሕፈት ቤት በቦሳሶ ከሚገኘው የዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት (IOM) ቅርንጫፍ ቢሮ ጋር በመተባባር 33 ፍልሰተኞች ከቦሳሶ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ አድርጓል።

ከተመላሾቹ መካከልም 12ቱ ሴቶች፣ 17ቱ ወንዶች እና 4ቱ ደግሞ ሕጻናት መሆናቸው ተገልጿል።

ወጣቶቹ በሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች ተታለውና ገንዘብ ከፍለው ከሀገራቸው ከወጡ በኋላ እንግልትና ስቃይ ሲደርስባቸው መቆየታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል።

ፑንትላንድ ያሉ ሕገ ወጥ ስደተኞችን የመመለሱ ተግባር እንደሚቀጥልም ነው የተገለጸው፡፡

በቀጣይ ሳምንት ሁለተኛ ዙር ተመላሾች ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመለሱም ተጠቁሟል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.