የሀገር ውስጥ ዜና

የአውሮፓ ሕብረት ለኢትዮጵያ ከ60 ሚሊየን ዩሮ በላይ የሰብዓዊ ድጋፍ ሊያደርግ ነው

By Amele Demsew

March 29, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 20፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ሕብረት 60 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ ለኢትዮጵያ የሰብዓዊ ድጋፍ ሊያደርግ መሆኑን በአዲስ አበባ የሕብረቱ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

ሕብረቱ በአጠቃላይ የ331 ሚሊየን ዩሮ ሰብዓዊ ድጋፍ ለአፍሪካ ቀንድ እንደሚሰጥ ይፋ ያደረገ ሲሆን÷ ይህም በዋናነት ለምግብ ዋስትና፣ ለተፈናቀሉ/ስደተኞች፣ ለአደጋ ዝግጁነት እንዲሁም ለትምህርት እንደሚውል ነው የተገለጸው፡፡

በመሆኑም ሕብረቱ ከዚህ ውስጥ በ2023 በግጭት እና በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ለሚደረጉ ሰብዓዊ ተግባራት ድጋፍ የሚውል ከ60 ነጥብ 5 ሚሊየን ዩሮ በላይ ገንዘብ በኢትዮጵያ ለሚያከናውነው የሰብዓዊ ረድኤት ስራ መመደቡ ተመላክቷል፡፡

ኢትዮጵያ ውስጥ ከ875 ሺህ በላይ ስደተኞች እንዳሉ ይታመናል፡፡

በተለይም ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ሱዳን የመጡ ስደተኞችን ተቀብላ እያስተናገደች መሆኗም ነው ተጠቆመው፡፡

ሕብረተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ እየሠራ መሆኑንም ገልጿል።