Fana: At a Speed of Life!

በልምምድ ላይ የነበሩ ሁለት የአሜሪካ የጦር  ሄሊኮፕተሮች ተከሰከሱ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአሜሪካ ኬንታኪ ግዛት በልምምድ ላይ የነበሩ ሁለት የአሜሪካ የጦር ሄሊኮፕተሮች መከስከሳቸውን የሀገሪቱ ጦር አስታውቋል፡፡

የአሜሪካ ጦር ቃል አቀባይ ኖንዲስ ቱርማን በሄሊኮፕተሩ ውስጥ የነበሩ የልምምድ ሰራተኞች  ቁጥር እና በሄሊኮፕተሩ መከስከስ  ያጋጠማቸው አደጋ በግልጽ አለመታወቁን አብራርተዋል፡፡

የበረራ አባላት በኬንታኪ ግዛት ትሪግ ካውንቲ በተባለው ስፍራ ከቀኑ 10 ሰዓት አካባቢ ሁለት “ብላክ ሃውክ” የተሰኙ ሄሊኮፕተሮችን እያበረሩ በነበረበት ወቅት መከስከሳቸውን ገልፀው÷የአደጋው መንስኤ በምርመራ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ይሁን እንጂ የኬንታኪ ግዛት አስተዳዳሪ አንዲ በሽር በትዊተር ገፃቸው እንዳስታወቁት ÷ በአደጋው ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች እንደሚኖሩ  ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የኬንታኪ ግዛት ፖሊስ እና የድንገተኛ አደጋ አስተዳደር ክፍል ለአደጋው ምላሽ እየሰጡ ነው ሲሉ አስተዳዳሪው መናገራቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.