Fana: At a Speed of Life!

ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ የሚደረግባቸውን ክትባቶች በሀገር ውስጥ ለማምረት ያለመ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዓመቱ ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ለግዢ ወጪ የሚደረግባቸውን ክትባቶች በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለማምረት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሄደ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ ክትባቶችን ለማምረት መሰራት በሚገባቸው  የጋራ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ኢትዮጵያ በየዓመቱ ለክትባቶች ግዢ የምታወጣውን ከ100 ሚሊየን ዶላር በላይ ወጪ ለማዳን ምርቶቹም በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በማምረት ለመተካት እንዲቻል ስራ ለመጀመር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያይዋል፡፡

ወደ ተግባር ለመግባት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም መግባባት ላይ መደረሱን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በ279 ሄክታር መሬት ላይ የተሰራው የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በህክምና ግብዓቶችና መድሃኒቶችን በማምረት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሃብቶች የተዘጋጀ የፋርማሲዩቲካል ፓርክ ነው፡፡

በአሁኑ ወቅትም ከ14 በላይ ባለሃብቶች በዘርፉ ተሰማርተው በመስራት ላይ ይገኛሉ፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.