Fana: At a Speed of Life!

“የምፅዓት ቀን ይከሰታል ሞት መፈናቀል ይኖራል” በሚል ስጋት በስደት ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል የተባሉት በመቶ የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን በኛንጋቶም ተገኙ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) “የምፅአት ቀን ይከሰታል ሞት መፈናቀል ይኖራል” በሚል ስጋት በመቶዎች የሚቆጠሩ ኡጋንዳውያን በስደት ኢትዮጵያ መግባታቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ መለስ አለም በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም ፥ “የምጽዓት ቀን ይመጣል” በሚል ስጋት ከቀያቸው ብዙ ኪሎ ሜትሮችን በመጓዝ በኢትዮጵያ በደቡብ ክልል ኛንጋቶም አካባቢ እንደሚገኙ ተናግረዋል፡፡

የኡጋንዳ ፖሊስ በቅርቡ ፥ በምስራቅ ሀገሪቱ ክፍል የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የምጽዓት ቀንን ሽሽት ከቀያቸው ወደ ኢትዮጵያ መሰደዳቸውን ገልጾ እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

ግለሰቦቹ የሚከተሉት ዕምነት መሪዎች የዓለም ፍጻሜ የሚጀምረው ከአካባቢያቸው መሆኑን መናገራቸውን ተከትሎ ሽሽታቸውን ወደኢትዮጵያ ማድረጋቸውንም ነው የሀገሪቱ ፖሊስ ያስታወቀው፡፡

በዚህም ቤት ንበረታቸውን በመሸጥ ለስደት እንደተዳረጉም የኡጋንዳ መገናኛ ብዙኃን ዘግበው ነበር።

#Ethiopia #Ngyangatom #Uganda

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.