የሀገር ውስጥ ዜና

ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ትብብራቸውን ለማጠናከር መከሩ

By Alemayehu Geremew

March 30, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ እና የዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት ትብብራቸውን ማጠናከር በሚችሉበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተሥፋዬ (ዶክተር) ከዓለም አቀፉ የሠራተኞች ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ጊልበርት ሃንግቦው ጋር ተወያይተዋል።

ውይይታቸው በጄኔቫ “ጥንቃቄ፣ ጥራት ያለው ሥራ እና የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ” በሚል መሪ ቃል ከፈረንጆቹ መጋቢት 27 ቀን ጀምሮ እየተካሄደ ከሚገኘው ዓውደ ጥናት ጎን ለጎን የተካሄደ ነው።

በዚህ ወቅት ኢትዮጵያ እና ዓለም አቀፉ የሰራተኞች ድርጅት ያላቸውን ትብብር ማጠናከር በሚችሉበት አግባብ ላይ መምከራቸውን በትዊተር ገጻቸው አስታውቀዋል።