የሀገር ውስጥ ዜና

የሀረሪ ክልል መስተዳድር ካቢኔ ውሳኔ አሳለፈ

By Feven Bishaw

March 30, 2023

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 21፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የሀረሪ ክልል መስተዳድር ካቢኔ በተለያዩ ረቂቅ ደንቦችና አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ።

ካቢኔው በዛሬው እለት ባካሄደው አስቸኳይ ውይይት ነው በተለያዩ ረቂቅ ደንቦችና አዋጆች ላይ ውሳኔ ያሳለፈው፡፡

ካቢኔው ተወያይቶ ውሳኔ ያሳለፈው በጠቅላይ አቃቤ ህግያን መተዳደሪያ ደንብና ማረሚያ ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ላይ ነው።

በዚህም መስተዳድር ምክር ቤቱ በጠቅላይ አቃቤ ህግያን መተዳደሪያ ደንብ በሙሉ ያፀደቀ ሲሆን÷ ማረሚያ ቤት ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅን ደግሞ ለክልሉ ምክር ቤት መምራቱን ከክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡